free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

አሏህ በፃፈልህ ተብቃቃ
ከሁሉም ሰዎች በፀጋ በላጭ ትሆናለህና


ይህ ርዕስ በተወሰነ መልኩ ባለፉት ምዕራፎች ውስጥ ተወድሷል። ሆኖም ግን የበለጠ ግልፅ እንዲሆን በዚህ ክፍል ውስጥ ቀለል ባለ መልኩ እደግመዋለሁ። አሏህ በሰጠህ ተክለሰውነት ፣ አቇም ፣ ገንዘብ ፣ ልጅ ፣ ቤትና ችሎታ መብቃቃት ይኖርብሃል። የቁርአንም መልእክት ከዚህ የተለየ አይደለም።

=<({አል-ቁርአን 7:144})>=

«የሰጠሁህንም ያዝ ፤ ከአመስጋኞችም ሁን።»

ቀደምቶቹ የኢስላም ምሁራን እና አብዛኞቹ የመጀመሪያው የኢስላም ትውልድ ሰዎች ድሆች ነበሩ። ብዙ ገንዘብ ፣ ውብ ቤቶች ፣ መሳፈሪያዎችና ጥበቃዎች አልነበራቸውም። ሆኖም ግን ህይወትን በሃብት ሞልተው ፤ ራሳቸውንና የሰው ልጆችን በሙሉ አስደስተው አለፉ። ምክንያቱም አሏህ የለገሳቸውን ፀጋ በትክክለኛው ቦታ ላይ ስላዋሉ፤ እድሜያቸውን ፣ ጊዜያቸውንና ችሎታቸውን አሏህ ባረከላቸው። ከነዚህ በተቃራኒ ደግሞ አሏህ ገንዘብ ፣ ልጆችና ብዙ ፀጋዎችን የሰጣቸው ሰዎችም ነበሩ። ሆኖም ግን እነዚያ ፀጋዎች ለመጥፋታቸው እና ለመከፋታቸው ምክኒያት ሆነው ህይወታቸውን አደፈረሱባቸው። ምክኒያቱም ከተስተካከለችው ተፈጥሮ እና ከእውነተኛው የህይወት ጎዳና ስለራቁ ነው። ይህም ቁሳቁሶች ስለበዙ ሰው ደስተኛ ሊሆን እንደማይችል የሚያመላክት ነው። ዓለም አቀፍ የምስክር ወረቀቶችን ይዘው በአስተሳሰባቸውና በስራቸው ከተራው ሰው ያልተለዩ ሆነው የሚኖሩም ብዙ ናቸው። በአንፃሩ ደግሞ ውስን ዕውቀት ኖሯቸው ሌሎችን ሲጠቅሙ ሲያቀኑ የሚስተዋሉም አሉ።

ደስታን የምትፈልግ ከሆነ አሏህ የሰጠህን አፈጣጠር ወደህ ተቀበለው። ቤተሰባዊ ሁኔታህን ፣ ድምፅህን ፣ የግንዛቤ ደረጃህንና ገቢህንም አትናቅ። እንዲሁም አንዳንድ ምሁራን ካለህ በታችም ቢሆን ወደህ መቀበል እንዳለብህ ይመክራሉ። ዱንያዊ ድርሻቸውን ትተው መኖርን ከመረጡ ኮከቦቹን ልዘርዝርልህ።

ዐጣዕ ቢን አቢ ረባህ በዘመኑ ታላቅ ምሁር የነበረ ሲሆን ጥቁር ፣ ባሪያ ፣ ፀጉረ ከርዳዳ ፣ አካለ ስንኩል ነበር። አል አሕናፍ ቢን ቀይስ የመላው አረቦች ታጋሽ የነበረ ሲሆን ሰውነቱ ቀጫጫ ፣ ወገበ ጎባጣ ፣ እግረ ደጋን ፣ አካለ ደካማም ነበር።

አል አዕመሽ በዘመኑ ምርጥ የሐዲስ አዋቂ ሲሆን ባሪያ ፣ ዓይነ ደካማ ፣ ድሃ ፣ ልብሱ የተቀደደ ፣ ገፅታውና ቤቱ የከሰሙ ነበር።

እንዲሁም የተከበሩና ከሁሉም የሰው ልጆች በላጭና የላቁ የነበሩት የአሏህ መልእክተኞች ሁላቸውም ፍየል ጠብቀዋል ፤ ዳውድ (ሰ.ዐ.ወ) የብረት ቀጥቃጭ ፣ ዘከሪያ አናፂ ኢድሪስም ልብስ ሰፊ ነበሩ።

ስለዚህ ደረጃህ የሚለካው ባለህ ችሎታ ፣ በመልካም ሥራህ ፣ ለሰዎች በምታበረክተው ጠቀሜታና በምታሳየው መልካም ስነ-ምግባር ነው። በመሆኑም ስላመለጠህ ውበት ፣ ገንዘብም ሆነ ልጆች አትተክዝ። አሏህ በሰጠህም ተብቃቅተህ በውዴታ ተቀበል።


601

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ


XtGem Forum catalog